ይህ ፓርክ የዞኑ 2ኛ ብሔራዊ ፓርክ ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማ አ/ምንጭ 195 ኪ.ሜ ፣ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ሃዋሳ በ248 ኪ.ሜ እንዲሁም ከሃገራችን ዋና ከተማ አ.አ በ468 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ፓርኩ 220 ኪ.ሜ ስኩዌር የቆዳ ስፋት ሲኖረው በውስጡም የተለያዩ ብዝሀ-ህይወትን ይዞ ይገኛል፡፡ ቁጫ፣ ደራማሎ፣ ዛላ፣ከምባና ደምባ ጎፋ ወረዳዎች ያዋስኑታል፡፡ እስካሁን በተደረገ ጥናት መሠረት 39 ትላልቅና መካከለኛ ዝርያ ያላቸው የዱርእንስሳት፣196 የአእዋፋት ዝርያዎች ተመዝግበዋል፡፡ ስዋይነስቆርኬ፣ፌቆ፣በሆር፣ጎሽ፣ከርከሮ፣ድኩላ፣ድፈርሳ፣ትልቁ አጋዘን፣የዱር ዓሳማ፣ዝንጀሮ፣ጦጣ፣ጉሬዛ፣አንበሳ ወዘተ በፓርኩ ይገኛሉ፡፡
ማዜ ብሔራዊ ፓርክ

Swayne’s Hartebeest’s
Tags: መዳረሻዎች