40ዎቹ ምንጮች

You are currently viewing 40ዎቹ ምንጮች

40ዎቹ ምንጮች ከአ/ምንጭ ከተማ በ5ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ተፈጥሮአዊ ቦታ ከ40 በላይ የሚሆኑ ምንጮች ከአለታማው ተራራ ሥር እየፈለቁ በመፍሰስ ለአካባቢው ልዩ ውበት ለግሰውታል፡፡ የምንጩ አካባቢ የተከለለና ጥቅጥቅ ባለደን የተሸፈነ በመሆኑ ቀዝቃዛና ነፋሻማ አየር በውስጡ አቅፎ የሚገኝ ሲሆን አካባቢውን ለሚጎበኙት ቱሪስት እርካታን ያስገኛሉ፡፡ የአርባምንጭ ከተማ ስያሜ የተገኘውም ከነዚህ የተፈጥሮ ምንጮች ሲሆን ለከተማዋ ነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚለግሱት እነዚሁ ምንጮች ናቸው፡

ምላሽ ይስጡ