አርባምንጭ አዞ ራንች

You are currently viewing አርባምንጭ አዞ ራንች

የአርባምንጭ አዞ ራንች ከአ/ምንጭ ከተማ በስተደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ 7 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በአባያ ሃይቅ ዳርቻ በ4ሄክታር የመሬት ስፋት ላይ በ1976 ዓ.ም የተቋቋመ ሰው ሰራሽ መስህብ ነው፡፡ የእርባታው ተግባር የሚከናወነው በሰው ሰራሽ ገንዳ ውስጥ ሲሆን አዞዎቹ በዕድሜ ልዩነት በተለያየ ገንዳ ውስጥ እንዲቀመጡ ይደረጋል፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ትልልቆቹ አዞዎች ትንንሾቹን እንዳይመገቧቸውና ጉዳት እንዳያደርሱባቸው ለመከላከል ነው፡፡ ራንቹ በአጠቃላይ ከ10000 በላይ አዞዎችን የማሳደግ አቅም ያለው ሲሆን በአሁኑ ወቅት ወደ 7000 የሚጠጉ አዞዎች በጣቢያው በማደግ ላይ ይገኛሉ፡፡

ምላሽ ይስጡ