የአዞ ገበያ

You are currently viewing የአዞ ገበያ

የአዞ ገበያ ከአ/ምንጭ ከተማ በ10ኪ.ሜ ርቀት በጫሞ ሐይቅ ላይ የሚገኝ መስህብ ነው፡፡ “አዞገበያ” የሚለው ሲያሜ ሲሰማ ምን አልባት አዞዎች የሚሸጡበትና የሚገዙበት ሊመስልዎ ይችላል፡፡ ነገሩ ወዲህ ነው፡አዞ ገበያ የሚለው ስያሜ የተገኘው በርካታ ቁጥር ያላቸው አዞዎች በአንድነት በአሸዋማው የጫሞ ሃይቅ ዳረቻ ተሰብስበው ፀሐይ የሚሞቁበት ቦታ ከመሆኑ በተጨማሪ ወፎች ከአዞዎች ጥርስ ስጋ የሚነቅሉበትና የምበሉበት ሁኔታን የሚገልጽ ስም ነው፡፡ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው አዞዎች፣ጉማሬዎችና አእዋፋት በዚህ ቦታ አንድ ላይ በሠላም አብረው በፍቅር ሲኖሩ ማየት ተአምር የሚያስብልና ማራኪ ትዕይንት ነው፡፡

ምላሽ ይስጡ