የነጭ ሣር ብሔራዊ ፖርክ ከአርባምንጭ ከተማ በ32 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ሲገኝ 514 ስኩዌር ኪ.ሜ ጠቅላላ ስፋት አለው፡፡ ፓርኩ የተቋቋመዉ 1967ዓ.ም ስሆን በፖርኩ ከ91 በላይ አጥቢ እንስሳት፣ከ351 በላይ አእዋፋት ሲገኙ ፖርኩ ከሚታወቅባቸው የዱር እንስሳት፡-ሜዳአህያ፣ድኩላ፣አጋዘን፣አንበሳ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው የስዋይነስ ቆርኬ ይገኙበታል፡፡ በሌላ በኩል በፖርኩ ውስጥ ከሚጠቃለሉት ተፈጥሮዊ መስህቦች እንደ ሰርመሌ ፍልውሃ፣40ዎቹ ምንጮች፣የተለያዩ የእጽዋትና የተለያዩ አገር በቀል ዛፎችን በውስጡ አጭቆ የያዘው የአርባምንጭ ደን፣የአዞ ገበያና የእግዜር ድልድይ በፖርኩ ውስጥ የሚገኙ ተጠቃሽ የቱሪስትመስህቦች ናቸው፡፡
ነጭ ሣር ብሔራዊ ፖርክ
